መልስ - ትርጉሙ፡- አላህ እሳቸውን አብሳሪና አስፈራሪ አድርጎ ለዓለማት የላካቸው መልዕክተኛው መሆናቸውን መመስከር ማለት ነው።
በዚህ ያመነ የሚከተሉት ነገሮች ግዴታ ይሆኑበታል፦
1- ያዘዙትን መታዘዝ፤
2- የተናገሩትን አምኖ መቀበል፤
3- እርሳቸውን አለማመፅ፤
4- እሳቸው በደነገጉት ካልሆነ በቀር አላህ አለማምለክ ነው። ይኸውም ሱናቸውን በመከተል እና ቢድዓን በመተው ነው።
የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ።} (ሱረቱ-አንኒሳእ፡ 80) ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፦ {ከልብ ወለድም አይናገርም። እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም። 4} [ሱረቱ-ነጅም 3፡4] ልዕለ ኃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ።21} [ሱረቱል አሕዛብ፡ 21]
መልስ-1- ተውሒድ አር-ሩቡቢያህ (የጌትነት አሀዳዊነቱ)፡- አላህ ብቸኛው የሁሉም ፈጣሪ፣ ለጋሽ፣ ባለቤትና ተቆጣጣሪ መሆኑን ማመን ነው።
2- ተውሒድ አል-ኡሉሂያ (የአምልኮ አሀዳዊነቱ)፡- በአምልኮ አላህን ብቻ ነጥሎ ማምለክ ነው። ከላቀው አላህ በስተቀር ማንም በሐቅ የሚመለክ የለም።
3- ተውሒዱል አስማእ ወስሲፋት (በስምና ባህርያቱ ያለው አሀዳዊነት)፡- በቁርአንና በሐዲሥ በተጠቀሱት የአላህ ስም እና ባህሪያቱ ያለ ምንም ምሳሌ መስጠት፣ ከፍጡራንም ጋ ሳያመሳስሉ እና ውድቅም ሳያደርጉ በቁርኣን እና ሱንና በተጠቀሰው መልኩ አምኖ መቀበል ነው።
ለሶስቱ የተውሒድ ዓይነቶች ማስረጃው ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {(እርሱ) የሰማያትና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው። እርሱን በመገዛትም ላይ ታገስ። ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን? 65} [ሱረቱ መርየም፡ 65]
መልስ- ሽርክ ማለት፦ የትኛውንም አይነት የአምልኮ መገለጫ ከላቀው አላህ ውጭ ላለ አካል አሳልፎ መስጠት ነው።
ዓይነቶቹ፦
ከባዱ ሽርክ ለምሳሌ፡- ከአላህ ውጭ ያለን አካል መማጸን ወይም ከርሱ ውጭ ላለ አካል መስገድ ወይም ከአሸናፊው አላህ ውጭ ላለ አካል እርድ ማቅረብ ነው።
(ትንሹ) መለስተኛው ሽርክ ለምሳሌ፡- ከአላህ ውጭ ባለ አካል መማል፣ ወይም ክታቦችን (ሕርዝ) አልያም መሰል ነገራቶችን ጥቅምን ለማምጣት ወይም ጉዳትን ለመከላከል በሚል እምነት ማንጠልጠል፣ ጥቂትም ቢሆን ሪያእ፣ ማለትም (ለይዩልኝ ብሎ መሥራት) ለምሳሌ ሰዎች እያዩት እንደሆነ አስቦ ሶላትን ማሳመር ይመስል።
መ - 1- በላቀው አላህ ማመን
2 - በመላእክቱ ማመን
3- በመጻሕፍቱ ማመን
4- በመልዕክተኞቹ ማመን
5 - በመጨረሻው ቀን ማመን
6- በቀደር መልካምም ሆነ መጥፎ በሆነ (የአላህ ቅድመ ውሳኔ) ማመን ናቸው።
ማስረጃውም፡- ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ነቢዩን - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን - ስለ እምነት የጠየቀበት የታወቀው በሙስሊም ዘገባ ውስጥ የሚገኘው ሶሒሕ ሐዲሥ ይገኝበታል፤ በሐዲሡም ጅብሪል ነብዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለ ኢማን ሲጠይቃቸው እንዲህ ብለውታል፦ “ስለኢማን ንገረኝ!” አላቸው። እርሳቸውም 'በአላህ፣ በመላእክቶቹ፣ በመጻሕፍቱ ፣ በመልእክተኞቹ፣ በመጨረሻው ቀንና ልታምን እና በቀደር ክፉም ሆነ ደግ ልታምን ነው።' አሉት።"
መልስ - በላቀው አላህ ማመን፡
§ አንተን የፈጠረህ፣ ሲሳይም የሚለግስህ፣ የፍጡራን ሁሉ ባለቤትና ገዥ አላህ መሆኑን ልታምን ነው።
§ በእውነት የሚመለከው እርሱው ነው፤ ከእርሱም ውጭ በእውነት ሊመለክ የሚገባው አምላክ የለም።
§ እርሱ ታላቅና ምሉዕ የሆነና ምስጋናም ሁሉ የተገባው ነው። ለእርሱም ውብ ስሞችና የላቁ ባህሪያት አሉት። ከፍጡራኑም ምንም ዓይነት ብጤም ሆነ አምሳያ የለውም።
በመላእክቶች ማመን፡
መላዕክት አላህ እርሱን እንዲያመልኩት ከብርሀን የፈጠራቸውና ለትእዛዙ ሙሉ በሙሉ ታዛዥ የሆኑ ፍጥረታት ናቸው።
- ከእነርሱ መካከል ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም የሚባል አለ፤ ለነብያት ራዕይን ይዞ የሚወርድ ነው።
በመጻሕፍቱ ማመን፡
ይህን ስንል አላህ ወደ መልእክተኞቹ ያወረዳቸው መጻሕፍቶችን ማለታችን ነው።
በነብዩ ሙሐመድ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ የወረደውን ቁርኣን።
በዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ በወረደው ኢንጅል።
በሙሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ በወረደው ተውራትን።
በዳውድ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ በወረደው ዘቡር።
በኢብራሂም እና በሙሳ ዓለይሂማ ሰላም ላይ በወረደው ሱሑፍ።
በመልዕክተኞች ማመን፡
ማለት እነዚያ ባርያዎቹን እንዲያስተምሩ፣ በመልካም እና በጀነት እንዲያበስሩ፣ ከክፉና ከእሳትም እንዲያስጠነቅቁ አላህ ወደ ፍጡራኑ የላካቸው መልዕክተኞች ናቸው።
ከመካከላቸው በላጮቹ፡- ኡሉ-ል-ዓዝም ሲሆኑ እነሱም፡-
ኑሕ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን
ኢብራሂም የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን
ሙሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን
ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን
ነብዩ ሙሐመድ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ናቸው።
በመጨረሻው ቀን ማመን፡
ይሀውም ሰዎች ከሞቱ በኋላ በመቃብር ውስጥ፣ በቂያማ ቀን፣ ከሞት በሚነሱበትና ፍርዳቸውንም በሚያገኙበት ቀን፣ የጀነት ሰዎች በመኖሪያቸው የጀሀነም ሰዎችም በመኖሪያቸው የሚሰፍሩበት ነው።
በቀደር ክፉውም ሆነ ደጉን ማመን፡
ቀደር፡- አላህ በአጽናፈ ዓለም ውስጥ የሚሆነውን ነገር ሁሉ እንደሚያውቅ፤ ያንንም በጥብቁ ሰሌዳ (በለውሐል መሕፉዝ) ላይ እንዳሰፈረው እና መገኘቱም ሆነ መፈጠሩ በእርሱ መሻት የሚከናወን መሆኑን ማመን ነው።
የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው።} [ሱረቱል ቀመር 49]
አራት እርከኖች አሉት፦
የመጀመርያው እርከን፡ ጥራት የተገባው አላህ የሆነውንም የሚሆነውንም ሁሉ አስቀድሞ ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑ
ማስረጃው ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {አላህ የሰዓቲቱ ዕውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው። ዝናብንም ያወርዳል። በማሕፀኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል። ማንኛይቱ ነፍስም ነገ የምትሠራውን አታውቅም። ማንኛይቱ ነፍስም በየትኛው ምድር እንደምትሞት አታውቅም። አላህ ዐዋቂ ውስጠ ዐዋቂ ነው። 34} [ሉቅማን፡ 34]
ሁለተኛው እርከን፡- አስቀድሞ የወሰነውንና የፈረደውን ሁሉ በለውሐል መሕፉዝ የመዘገበው መሆኑን ማመን ነው። በመሆኑም የተከሰተውም ይሁን የሚከሰተውም ሁሉ እርሱ ዘንድ ባለው መጽሐፍ ሰፍሯል።
ማስረጃው ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {የሩቅ ነገርም መክፈቻዎች እርሱ ዘንድ ናቸው። ከእርሱ በቀር ማንም አያውቃቸውም። በየብስና በባሕር ያለውንም ሁሉ ያውቃል። ከቅጠልም አንዲትም አትረግፍም የሚያውቃት ቢሆን እንጅ። ከቅንጣትም በመሬት ጨለማዎች ውስጥ የለም ከእርጥብም ከደረቅም አንድም የለም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውሰጥ (የተመዘገበ) ቢሆን እንጅ። 59} [ሱረቱል አል-አንዓም 59]
ሦስተኛው እርከን፡ ነገራቶችን ሁሉ እውን የሚሆኑት በእርሱ መሻት ነው። በመሆኑም በእርሱ ፈቃድ ካልሆነ በቀር ከእርሱም ሆነ ከፍጥረቱ የሚከሰት ምንም ዓይነት ነገር የለም።
ማስረጃው ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {ከናንተ ቀጥተኛ መሆንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)። 28 የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም። 29} [ሱረቱ-አትተክዊር፡28-29]
አራተኛው እርከን፡- ነገራቶችን ሁሉ የፈጠረው እርሱ መሆኑን ማመን ነው። ራሳቸውን፣ ባህሪያቸው፣ እንቅስቃሴዎቻቸውና በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ የፈጠረው እርሱ ነው።
ማስረጃው ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {«አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲሆን።» 96} [ሱረቱ-አስሷፍፋት 96]
መልስ - በነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እና በባልደረቦቻቸው ጊዜ ያልነበረ ሰዎች በሃይማኖት ላይ የፈለሰፉት አዲስ ፈሊጥ ሁሉ ቢድዓህ ይባላል።
* ላመጣው ሰው እንመልስለታለን (እናወግዘዋለን) እንጅ አንቀበለውም።
ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ስላሉ፡- "ቢድዓ (አዲስ ፈሊጥ) ሁሉ ጥመት ነው።" አቡዳውድ ዘግበውታል።
ለምሳሌ፡- በዒባዳ ላይ መጨመር: ውዱእ ላይ ለአራተኛ ጊዜ ማጠብ እና የነብዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ልደት (መውሊድ) ማክበርን ፤ ይህ ሁሉ ተግባር ከነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ይሁን ከባልደረቦቻቸው የተገኘ ምንም መሰረት የለውም።
መልስ- ወላእ ሲባል፡- ምእመናንን መወዳጀትና መደገፍ ነው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው።} [ሱረቱ አትተውባህ፡ 71]
አል በራእ ሲባል ደግሞ፡ ከሓዲያንን የኢስላም ጠላትነታቸውን አውቆ ጠላት አድርጎ መያዝ ነው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {በኢብራሂምና በእነዚያ ከእርሱ ጋር በነበሩት (ምእምናን) መልካም መከተል አለቻችሁ። ለሕዝቦቻቸው «እኛ ከእናንተ ከአላህ ሌላ ከምትግገዘትም ንጹሖች ነን። በእናንተ ካድን። በአላህ አንድ ብቻ ሲኾን እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ።» ባለ ጊዜ (መልካም መከተል አለቻችሁ)።} [ሱረቱል ሙምተሒናህ፡ 4]
መልስ-
1- ከባዱ ኒፋቅ፡- ላይ ላዩን አማኝ መስሎ ክህደትን በውስጥ መደበቅ ነው።
ከእስልምና የሚያስወጣ ሲሆን ከከባዱ የክህደት ዓይነትም ነው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው። ለእነሱም ረዳትን አታገኝላቸውም። 145} [ሱረቱ አንኒሳእ፡ 145]
2 - መለስተኛ ሙናፊቅነት:
እንደ መዋሸት፣ ቃል ኪዳንን ማፍረስ እና እምነት መክዳት ያሉት ናቸው።
ከእስልምና የሚያስወጣ ባይሆንም ባለቤቱን ለቅጣት የሚዳርግ ኃጢአት ነው።
የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "የሙናፊቅ ምልክቱ ሶስት ነው፤ ሲናገር ይዋሻል፣ ቃል ሲገባ ቃሉን ያፈርሳል፣ ሲታመን ይክዳል።" ቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል።
መልስ- ሶሓባ የሚባለው፡- ነብዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አማኝ ሆኖ አግኝቷቸው በእስልምና ላይ ሆኖ የሞተ ነው።
ሶሓቦችን እንወዳቸዋለንም ፋናቸውንም እንከተላለን፤ እነርሱ ከነብያት በኋላ ከሰዎች ሁሉ በላጭ ናቸው።
ከመካከላቸው በላጮቹ አራቱ ኸሊፋዎች (ቅን ምትኮች) ሲሆኑ እነርሱም፡-
አቡበክር አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው
ዑመር አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው
ዑሥማን አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው
ዐሊይ አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው
መልስ- አላህን መፍራት ሲባል፡- አላህን እና ቅጣቱን መፍራት ነው።
ተስፋን አላህ ላይ ማድረግ ሲባል ደግሞ፡ የአላህን ምንዳ፣ ይቅር ባይነት እና ምሕረትን ተስፋ ማድረግ ነው።
ማስረጃው ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {እነዚያ እነርሱ የሚግገዟቸው ማንኛቸውም (ወደ አላህ) በጣም ቀራቢያቸው ወደ ጌታቸው መቃረቢያን (ሥራ) ይፈልጋሉ። እዝነቱንም ይከጅላሉ። ቅጣቱንም ይፈራሉ። የጌታህ ቅጣት የሚፈራ ነውና።} [ሱረቱል ኢስራእ፡ 57] የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው። 49 ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መሆኑን (ንገራቸው)። 50} [ሱረቱል ሒጅር፡ 49-50]
መልስ- አላህ፡- ትርጉሙም ተጋሪ የሌለው ብቸኛው በእውነት የሚመለክ አምላክ ማለት ነው።
አር-ረብ፡- ትርጉሙም ጥራት የተገባው አምላካችን አላህ ብቸኛው የሁሉም ፈጣሪ፣ ባለቤት፣ ሰጪና አስተናባሪው ማለት ነው።
አስ-ሰሚዕ፡- የመስማት ችሎታው ሁሉንም ነገር የሚያካልል እና በዓይነትም በብዛት የተለያዩ የሆኑ ድምፆችን በሙሉ የሚሰማ ማለት ነው።
አል-በሲር፡ ሁሉንም ነገር የሚያይ እና ትንሹም ይሁን ትልቁን ሁሉ የሚመለከት ነው።
አል-ዓሊም፡ እውቀቱ ያለፈውን፣ የአሁኑንና የወደፊቱን ሁሉ ያካለለ ነው።
አር-ረሕማን፡ እዝነቱ ለእያንዳንዱ ህያው ፍጡር ሁሉ የተዘረጋ ሲሆን ፍጡራን ሁሉ በእዝነቱ ስር ናቸው።
አር-ረዛቅ፡- የሰውም፣ የጂንም እና የተንቀሳቃሽ ህያው ሁሉ ሲሳይ እርሱ ዘንድ የሆነ ነው።
አል-ሓይ፡- የማይሞት ህያው የሆነ ነው። ፍጥረታት ሁሉ ሟች ናቸው።
አል-ዓዚም፡ በስሙም በባህሪያቱም እንዲሁም በድርጊቶቹም ፍጹምነት እና ልዕልና ያለው ነው።